ከቪዛ እና ፓስፖርት ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን ለማግኘት የትኛውን ድረ-ገፅ እንጠቀም? 

ይህ ጥያቄ በተደጋጋሚ ሲነሳ ይታያል፣ ምክንያቱ ደግሞ አገልግሎቱን እንሰጣለን የሚሉ በርካታ ተመሳስለው የተከፈቱ ድረ-ገፆች መኖራቸው ነው። 

ለምሳሌ ያክል ethiopiaevisa፣ ethiopiaonlinevisa፣ evisaforethiopia የሚሉ ድረ-ገፆች የቪዛ አገልግሎቶችን እንሰጣለን ቢሉም ሀሰተኛ እንዲሁም በመንግስት እውቅና የሌላቸው ናቸው። 

ለፓስፖርት አገልግሎቶች ትክክለኛው ድረ-ገፅ: https://www.invea.gov.et/ 

ለኢ-ቪዛ: 

https://www.evisa.gov.et/

ተመሳስለው ከሚከፈቱ የማህበራዊ ሚድያ ገፆች እንዲሁም ድረ-ገፆች ራሳችንን እንጠብቅ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::