“የዩራኒየም ማእድን በኢትዮጵያ ተገኘ” በሚለው መረጃ ዙርያ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ምን ይላል?

ሰሞኑን “ሰበር ዜና” በማለት በርካታ ግለሰቦች፣ የፌስቡክ ገፆች እና አንዳንድ ዲጂታል ሚድያዎች “ለኒውክሌር ማብላያ የሚሆነው የዩራኒየም ማእድን በኢትዮጵያ ተገኘ” የሚል መረጃ ሲያጋሩ ነበር። ይህን መረጃ እንድናጣራም በርካታ መልእክቶች ደርሰውናል። 

ይህን መረጃ ለማጣራት የማእድንና ነዳጅ ሚኒስትር የሆኑትን ኢ/ር ታከለ ኡማን ኢትዮጵያ ቼክ አነጋግሯል። 

ኢ/ር ታከለ ለኢትዮጵያ ቼክ እንዳብራሩት መንግስት ይህ ዩራኒየም የተባለ ማእድን ይገኝበታል ተብለው የተገመቱ ቁልፍ ቦታዎች ላይ ምርመራ እያረገ ይገኛል። 

“ጂኦሎጂስቶቻችን ላለፉት 10 ወራት መጠነ ሰፊ ምርመራ እያረጉ ቆይተዋል፣ አሁንም እያረጉ ይገኛሉ። ስለዚህ ጥናቱ ባልተጠናቀቀ ጉዳይ ላይ አሁን ላይ [እንደተረጋገጠ አርጎ] ማውራቱ ትክክል አይሆንም” የሚል መልስ ሰጥተዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::