ትክክለኛዎቹ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አካውንቶች የትኞቹ ናቸው? 

ከ14,000 በላይ ተከታይ ያለው በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስም የተከፈተ የፌስቡክ ገፅን ጨምሮ በርከት ያሉ የፌስቡክ እና ቴሌግራም አካውንቶች በድርጅቱ ስም እና አርማ መኖራቸውን ተመልክተናል። 

ከጥቂት ወራት በፊት በቴሌኮም ዘርፍ ስራውን በኢትዮጵያ ለመጀመር ስምምነት የገባው እንዲሁም ፈቃድ ያገኘው ይህ ድርጅት ከፍቷቸዋል የተባሉት እነዚህ ገፆች እና አካውንቶች በብዙ ኢትዮጵያውያን ስራ ፈላጊዎች ዘንድ እየተዘወተረ መሆኑንም ለመታዘብ ችለናል። 

እ.ኤ.አ. በ2022 ስራውን በኢትዮጵያ የሚጀምረው ይህ ኩባንያ በተረጋገጠው የትዊተር አካውንቱ ላይ ባስቀመጠው መልዕክት ከ’LinkedIn’ ውጪ የድርጅቱ መለያዎች በሙሉ @SafaricomET የሚል አድራሻ እንዳላቸው እና ከዚያ ውጪ ያሉት በሙሉ ግን ተመሳስለው የተከፈቱ መሆናቸውን አስታውቋል። 

“ምንም አይነት መረጃዎችን ከኛ ጋር ተመሳስለው በተሰሩ ገጾች ላይ አያስተላልፉ” ሲልም ምክር ይሰጣል። ትክክለኛዎቹ የድርጅቱ አካውንቶች እነዚህ ናቸው: 

ትዊተር: https://twitter.com/SafaricomET

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/SafaricomET/ 

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራስዎን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::