ትዊተር በመላው አለም የአገልግሎት መቋረጥ አጋጠመዉ

ትዊተር በመላው አለም የአገልግሎት መቋረጥ ከደቂቃዎች በፊት ገጥሞት እንደነበር ተመልክተናል!

የድረ-ገጾችንና መገልገያዎችን አሁናዊ ሁኔታ የሚከታተለው ዳውንዲቴክተር (Downdetector) የትዊተር አገልግሎት ከቀኑ 9 ሰዐት ከ05 ደቂቃ ጀምሮ ተቋርጦ እንደነበር ያመለከተ ሲሆን ከመላው ዓለም ከ27 ሺህ በላይ ሪፖርቶችን መቀበሉን አስታውቋል።

የኢንተርኔት ኔትወርክን አሁናዊ ሁኔታ የሚከታተለው ኔትብሎክስ (NetBlocks) በበኩሉ አገልግሎቱ የተቋረጠው በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደነበር አረጋግጧል።

አገልግሎቱ 9 ሰዐት ከ37 ደቂቃ ላይ እንደገና መመለሱን ተመልክተናል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::