“በደብዳቤው ላይ የተገለጹት ሁለት መልዕክቶች በ2014 ዓ/ም የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና ላይ ይተገበራሉ”— የትምህርት ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ቼክ

“የ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተናን ይመለከታል!” የሚል ርዕስ ያለውና በትምህርት ሚኒስቴር እንደተጻፈ የሚገልጽ ደብዳቤ በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የተመለከቱ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮች ደብዳቤው ትክክለኛ መሆኑን እንድናጣራላቸው ጠይቀውናል።

ደብዳቤው የ2014 ዓ/ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የትምህርት ይዘት እንደሚሸፍን እንዲሁም የኢኮኖሚክስ ትምህርት ፈተና እንደማይሰጥ ይገልጻል።

ኢትዮጵያ ቼክ የደብዳቤውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ትምህርት ሚኒስቴርን አነጋግሯል። በሚኒስቴሩ የስርዐተ ትምህርት ዝግጅትና ምርምር ጄነራል ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ ደብዳቤው ትክክለኛ መሆኑንና ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች መላኩን ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል።

ዳይሬክተሩ በደብዳቤው ላይ የተገለጹት ሁለት መልዕክቶች በ2014 ዓ/ም የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና እንደሚተገበሩም አጽኖት ሰጥተዋል።

በደብዳቤው ላይም ተማሪዎች ይህን አውቀው መዘጋጀት እንዳለባቸው ተጠቅሷል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::