ኢትዮጵያ ቼክ መጠይቅ ትንተና

ኢትዮጵያ ቼክ በትናንትናው እለት “ለእርስዎ የትኛው የመረጃ ምንጭ በአንፃራዊነት የተሻለ ተአማኒነት አለው?” የሚል ጥያቄ ለተከታታዮቹ ቴሌግራም ላይ አቅርቦ ነበር።

በውጤቱም 42% የማምነው የመረጃ ምንጭ የለም፣ 26% የውጭ ሚድያዎች፣ 25% የግል ሚድያዎች፣ 18% የመንግስት ሚድያዎች፣ 14% በግል ወይም በቡድን የሚፅፉ (ጦማሪዎች) እንዲሁም 11% ዲጂታል (online) ሚድያዎች ብለው ድምፅ ሰጥተዋል። በአጠቃላይ ከ1,700 በላይ ሰዎች ድምፅ በመስጠት ተካፍለዋል።

በርከት ያሉ ሰዎች የመረጡት “የማምነው የመረጃ ምንጭ የለም” የሚለው ምርጫ በግልፅ እንደሚያመለከተው ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ ነው ብሎ አምኖት የሚቀበለው መረጃ ማጣት እየተበራከተ እየመጣ እንደሆነ ያመለክታል። ይህም ከሀሰተኛ መረጃ ስርጭት መስፋፋት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው መናገር ይቻላል።

ህብረተሰቡ ትክክለኛ ለማግኘት በተቸገረበት በዚህ ወቅት ሚድያዎች ተአማኒነታቸው በእጅጉ የቀነሰ መሆኑ ይታያል፣ ይህም ለሚፈጠሩ ችግሮች ዋና መንስኤ ነው ባይባል እንኳን በማባባስ ደረጃ ከፍተኛ ተፅእኖ ይኖረዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::