በየወሩ እየተጋራ የሚገኝ ሀሰተኛ የስክሪን ቅጂ!

ይህ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ስም እና ምስል ተቀናብሮ እየተሰራጨ ያለ መረጃ የሀሰት እንደሆነ ከሳምንታት በፊት መረጃ አጋርተን ነበር።

ይህ ልጥፍ በጥር፣ መጋቢት እና ሚያዝያ ወሮች ውስጥ በተለያዩ አካውንቶች ሼር ተደርጓል። በስክሪን ቅጂው ላይ እንደሚታየው ልጥፉ የፎቶሾፕ ቅንብር ነው፣ ለፎቶሾፕ ቅንብር የተጠቀሙበት የፊደል አይነትም (font) የፌስቡክ አይደለም።

የሰዎችን፣ የድርጅቶችን ወይም የሌሎችን የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችን ፅሁፍ አስመስሎ ማቅረብ እየተለመደ መጥቷል። ብዙዎችም ይህን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሲያጋሩ ይታያል።

ስለሆነም ትክክለኛ የሶሻል ሚድያ ልጥፎችን በማስመሰል ከሚቀርቡ ፖስቶች፣ ትዊቶች እና መልዕክቶች መጠንቀቅ ይገባል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚወጡ ነገሮች ሁሉ እውነት ወይም ትክክለኛ እንዳልሆኑም መገንዘብም አስፈላጊ ነው።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::