በፖላንድ የትምህርት እድል እንደተገኘ በማስመል እየተሰራ ያለ የማጭበርበር ድርጊት! 

ፖላንድ ሀገር በሚገኘው WSB ዩኒቨርሲቲ የትምህርት እድል እንደተገኘ በማስመል ደብዳቤ በመስራት ሰዎችን የማጭበርበር ስራ እየተሰራ እንደሆነ ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል፣ በድርጊቱ ላይም ኢትዮጵያውያን ጭምር እየተሳተፉም ይገኛሉ። 

የትምህርት እድሉን ለማግኘት 600 ዩሮ ክፍያ የሚጠይቁ ሲሆን ክፍያው ቶሎ ካልተፈፀመ እድሉ እንደሚያመልጥ በመናገር ሊያግባቡ ይሞክራሉ፣ በርካቶችም የዚህ ሰለባ ሆነዋል። 

ኢትዮጵያ ቼክ ይህን ፖላንድ የሚገኝ ዩኒቨርሲቲን መረጃ የጠየቀ ሲሆን ኦስካር ጃደር የተባሉ የተቋሙ ባልደረባ ደብዳቤው የተቋሙ እንዳልሆነ አረጋግጠዋል (ኢሜይሉ ምስሉ ላይ ተያይዟል)። 

በትምህርት፣ በስራ እና በጉዞ ስም ከሚከናወኑ የማጭበርበር ድርጊቶች ራሳችንን እንጠብቅ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::