ዛሬ የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀን “ጋዜጠኝነት በዲጂታል ከበባ ውስጥ”  (Journalism Under Digital Siege) በሚል መሪ-ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ በመከበር ላይ ይገኛል። 

የዘንድሮው መሪ-ቃል በተለምዶ በጋዜጠኞች ላይ ከሚደርሰው አካላዊና መሰል ጥቃቶች ባሻገር ጋዜጠኞች ስራቸውን በሚከውኑበት ወቅት በዲጅታል ምህዳር የሚደርሱባቸውን የደህንነት ስጋቶች አጽኖት ለመስጠት ያለመ ነው። 

ጋዜጠኞች በዲጅታል ዓለም ከሚያጋጥሟቸው የደህንነት ስጋቶች መካከል መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ አካላት የሚደረግ ስለላና ክትትል ይጠቀሳሉ። እነዚህ ድርጊቶችም ወደ አካላዊ የደህንነት ስጋቶች የሚያመሩ ሲሆን ጋዜጠኞችን የመረጃ ምንጫቸውን እንዲሁም መገልገያ መሳሪያዎቻቸውን ለአደጋ ያጋልጣሉ። 

በተጨማሪም ጋዜጠኞች በዲጂታል ምህዳር ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎችን የሚደርሷቸው ሲሆን ይህም ስራቸውን ተረጋግተው እንዳይሰሩ ትልቅ እክል ይሆንባቸው። 

የጋዜጠኞች በአካላዊም ይሁን በዲጂታል ደህንነት ስጋት ውስጥ መውደቅ ሀሠተኛና የተዛባ መረጃ ለሚያሰራጩ አካላት ባዶ ቦታ እንደሚፈጥር እሙን ነው። 

ስለሆነም ዛሬ የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን ስናከብር ጋዜጠኞች በዲጅታል ምህዳር ውስጥ በሚደርስባቸውን የደህነንት ስጋት ተዋናይ ላለመሆን እና የዲጂታል ከበባው እንዲፍታታ የራሳችንን አስተዋጽዖ ለማበርከት ቃል በመግባት እንዲሆን ኢትዮጵያ ቼክ ጥሪውን ያስተላልፋል። 

የሚዲያ ተቋማት መሪዎችና ጋዜጠኞችም ለሳይበር ደህንነት ትኩረት እንዲሰጡ መልክታችን ነው። 

መልካም የፕሬስ ነጻነት ቀን!

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::