ዋትስአፕ የደህንነት ድጋፍ እና አፕዴትን በተመለከተ በመተግበርያው ዙርያ ያወጣው አዲስ መረጃ!

የመልዕክት አገልግሎት በመስጠት የሚታወቀው የዋትስአፕ (WhatsApp) መተግበሪያ እ.አ.አ ከህዳር 1 2021 ዓ.ም ጀምሮ ቆየት ያለ ሶፍትዌር ባላቸው ስልኮች የደህንነት ድጋፍ (security support) እና አፕዴት ማድረግ እንደሚያቆም በድረ-ገጽ አስነብቧል። በተጨማሪም ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ቆየት ባሉ በርካታ የስልክ ሞዴሎች ዋትስአፕን መጫን፣ አፕዴት ማድረግና የደህንነት ድጋፍ ማድረግ እንደሚያቋርጥ በፌስቡክ ስር የሚተዳደረው ዋትስአፕ አስታውቋል።

ዋትስአፕ እንዳስታወቀው ድጋፉ የሚቋረጥባቸው ለአንድሮይድ 4.0.3 እና ከዛ በታች እንዲሁም ለአይፎን ከiOS 9 እና ከዛ በታች የሆኑ ሶፍትዌሮችን ለሚጠቀሙ ስልኮች ነው።

ከመተግበሪያው ድጋፍ የሚቋረጥባቸው የስልክ ሞዴሎች ደግሞ ከሳምሰንግ Samsung Galaxy Trend Lite, Galaxy Trend II, Galaxy SII, Galaxy S3 mini, Galaxy Xcover 2, Galaxy Core, Galaxy Ace 2 ZTE Grand S Flex ሲሆኑ ከዜድቲኢ ደግሞ ZTE V956, Grand X Quad V987, and ZTE Grand Memo ናቸው። እንዲሁም ከሁዋዌ Ascend G740, Ascend Mate, Ascend D Quad XL, Ascend D1 Quad XL, Ascend P1 S, Ascend D2 ፤ ከሶኒ Xperia Miro, Sony Xperia Neo L, Xperia Arc S የተባሉ የስልክ ሞዴሎች ይገኙባቸዋል።

በተጨማሪም የኤልጂ፣ የሌኖቮ፣ አልካቴልና የሌሎች ስልክ አምራች ድርጅቶች ስሪት የሆኑ ቆየት ያሉ ሞዴሎች ድጋፍ ማግኘታቸው እንደሚቋረጥ ዋትስአፕ ገልጿል። ዋትስአፕ እንደሚለው ከላይ የተዘረዘሩት የስልክ ሞዴሎች ተጠቃሚ የሆኑ የመተግበሪያው ደንበኞች በዋትስአፕ መገልገል መቀጠል የሚችሉ ሲሆን የደህንነት ድጋፍና አፕዴት ማግኘት አይችሉም። እንዲሁም ገንዘብ ማስተላለፍን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችንም መጠቀም አይችሉም።

በዚህም መሰረት የዋትስአፕ ተጠቃሚ ከሆኑና ስልክዎት ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ የደህንነት ድጋፍ እንዲሁም አፕዴት የማግኘትዎ ነገር ይቋረጣል ማለት ነው። ስለሆነም አገልግሎቶቹን ለማስቀጠል የስልክዎን እና የሶፍትዌሮችን ደረጃ ከፍ ማድረግ ይጠበቅቦታል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::