ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ወደ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን!

“የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ” በሚል ስያሜ ይታወቅ የነበረው የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤት የፌስቡክ ገጽ ስያሜው ወደ “የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን” መቀየሩን ያስተዋሉ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታዮች የመሥሪያ ቤቱ ስያሜ ስለመቀየሩ እንድናጣራላቸው ጠይቀውናል።

ኢትዮጵያ ቼክ የስም ለውጡን በተመለከተ መሥሪያ ቤቱን አነጋግሯል።

የመሥሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ትዕግስት አሞኘ ኤጀንሲው ከወራት በፊት ወደ ባለስልጣን መሥሪያ ቤትነት ማደጉን ገልጸው ይህም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌደራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1263/2014 መሰረት መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህም የመሥሪያ ቤቱ ስም ከኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ወደ የኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የሚል ስያሜ ተቀይሯል፡፡

ኢትዮጵያ ቼክ አዋጁን የተመለከ ሲሆን ከየሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በተጨማሪም የሌሎች የፌድራል መንግስት መሥሪያ ቤቶች ስምና ተጠሪነት መቀየሩን አስተውሏል።

አዋጁ በባልስልጣን የሚል ስያሜ ያላቸው መሥሪያቤቶች የቁጥጥር፤ ደረጃ የማውጣትና በወጣው ደረጃ መሰረት መተግበሩን የማረጋጥ፣ በዋናነት በተሰጣቸው የዘርፍ ስራ ስታንደርዶችን የማውጣት፤ ስታንደርዶችን መሰረት በማድረግ የቁጥጥር ስራ የማከናውን፤ ወይም በሚመለከተው አካል የወጡ ስታንዳርዶችን የማስፈፀም፣ ፍቃድ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ሲኖር ፍቃድ የመስጠት እና የመቆጣጠር ሥራን የማከናውን ስልጣን እንዳላቸው ደንግጓል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተጠሪነቱ ለፍትህ ሚንስቴር መሆኑም በአዋጁ ተደንግጓል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::