“ከሰሞኑ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ከ200 በላይ ዜጎች ተገድለዋል”— የሰሜን ጎንደር ዞን ጤና ቢሮ ሀላፊ እንዲሁም የዳባት ወረዳ አስተዳዳሪ ለኢትዮጵያ ቼክ

ከሰሞኑ በሰሜን ጎንደር ዞር ባሉ የተለያዩ ስፍራዎች የህወሀት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ከ200 በላይ ሰላማዊ ዜጎች ህይወታቸውን እንዳጡ የሰሜን ጎንደር ዞን የጤና ቢሮ ሀላፊ እንዲሁም የዳባት ወረዳ አስተዳዳሪ ለኢትዮጵያ ቼክ ተናግረዋል።

በአንዳንድ አለም አቀፍ ሚድያዎች በዚህ ጥቃት 123 ዜጎች ህይወታቸውን እንዳጡ ቢገለፅም ቁጥሩ ከ200 በላይ እንደሆነ የጤና ቢሮው ሀላፊ አቶ በቀለ ይትባረክ ለኢትዮጵያ ቼክ አስረድተዋል። “ይህ በአይናችን ያየነው ነው፣ በህወሀት ታጣቂዎች በተለይ ነሀሴ 28 እና 29 የተገደሉ ተጨማሪ ሰዎች እንደሚኖሩ ስለተገመተ ፍለጋው ቀጥሏል” ብለዋል።

የዳባት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሰውነት ውባለም በበኩላቸው “ጎንደር ለመግባት አስበው የነበሩት ታጣቂዎች ሳይሳካላቸው ሲቀር ሲቪሎች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል፣ ዝርፊያ አድርገዋል” ያሉ ሲሆን በተለይ በጨና ቀበሌ ላይ ከፍተኛ ግፍ ተፈፅሟል ብለዋል።

አለም አቀፍ ሚድያዎች የደረሳቸው 123 የሚለው የሟቾች ቁጥር የመጀመርያ ሪፖርት እንደነበር ገልፀው ቁጥሩ አሁንም እያሻቀበ እንደሆነ ለኢትዮጵያ ቼክ አስረድተዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::