በዋልታ የፌስቡክ ገጽ ላይ የደረሰዉን ጥቃት በተመለከተ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዛሬ ተጨማሪ መረጃ አጋርቷል!

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ችግሩ የተፈጠረው “ከአድሚኖች እና ኤዲተሮች ጋር የተያያዘ ጥቃት ነው” ብለው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አብራርተዋል።

በዋናነት ለጥቃቱ ሁለት ምክንያቶችን ያስቀመጡት ዋና ዳይሬክተሩ አንዱ የዋልታ የፌስቡክ ገጽ ዋና አድሚን ሃገር ዉስጥ ካለመሆኑ ጋር የተያያዘ እንደሆነ እና ሁለተኛዉ ምክንያት ደግሞ የሚዲያዉን የፌስቡክ አካዉንት አክሰስ እንዲያደርጉ ሃላፊነት በወሰዱ አካላት ስህተት በተለይም አንዱ የፌስቡክ ኤዲተር የተላከለትን አጥፊ ተልእኮ ያለዉን ሊንክ ያለ ጥንቃቄ በመክፈት ለመረጃ ጥቃቱ መፈጸም ሚና እንደነበረዉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ሊደረጉ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ከቀናት በፊት አጋርቶ ነበር። ከሰሞኑ በስፋት ተግባር ላይ እየዋለ ካለ ከዚህ የማጭበርበርያ ዘዴ አሁንም እንድንጠነቀቅ በማሳሰብ ሊንኩን በድጋሜ ለማጋራት ወደድን: https://t.me/ethiopiacheck/1075

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::