ቲክቶክ ላይ ተገቢ ያልሆኑ ቪድዮዎችን እንዴት ሪፖርት ማረግ ይቻላል?

የአጭር ተንቀሳቃሽ ምስል ማጋራት አገልግሎት የሚሰጠው ቲክቶክ በተለይ ልዩ ተሰጥዖና ሙያ ባላቸው ግለሰቦች እንዲሁም ለመዝናናትና ለመማር በሚፈልጉ ተጠቃሚዎች ዘንድ ተመራጭ የማህበራዊ ሚዲያ እየሆነ መጥቷል።

በዚህም በመላው ዓለም በርካታ ደንበኞችን ማፍራት ችሏል። በሀገራችንም ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ የቲክቶክ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ማስተዋል ችለናል።

በቲክቶክ ልዩ ተሰጧቸውንና ሙያቸውን ከሚያጋሩ ተጠቃሚዎች ጎን ለጎን የጥላቻ መልዕክት፣ የሀሠተኛና የተዛባ መረጃ የሚያሰራጩ እንዲሁም የማጭበርበር ድርጊት የሚከውኑ መኖራቸውን አይተናል። እንዲህ ያሉ የቲክቶክ ተጠቃሚዎች ሲያጋጥሙን ሪፖርት በማድረግ አሉታዊ ሚናቸውን መቀነስ እንችላለን። ሪፖርት ለማድረግም ቲክቶክ ቀለል እና በርከት ያሉ አማራጮች አሉት።

1. ቪዲዮ ሪፖርት ለማድረግ:-
•ሪፖርት ለማድረግ ወደፈለጉት ቪዲዮ ይሂዱ፤
•ቪዲዮውን ተጭነው ትንሽ ይቆዩ፤
•ቀጥሎ “Report” የሚለውን ይጫኑ፤ ከዚያም መመሪያዎችን ይከተሉ።

2. በቀጥታ በመተላለፍ ላይ ያለን ቪዲዮ (Live Video) ሪፖርት ለማድረግ፦
•በቀጥታ በመተላለፍ ላይ ወደሚገኘው ቪዲዮ ይሂዱ፤
•ከዚያም “Share” የሚለውን ይጫናኑ፤
•ቀጥሎ “Report” የሚለውን ይጫኑ፤ ከዚያም መመሪያዎችን ይከተሉ።

3. አስተያየትን (comment) ሪፖርት ለማድረግ፦
•ሪፖርት ማድረግ ወደፈለጉት አስተያየት ይሂዱ፤
•አስተያየቱ ላይ ተጭነው ትንሽ ይቆዩ፤
•ቀጥሎ “Report” የሚለውን ይጫኑ፤ ከዚያም መመሪያዎችን ይከተሉ።

4. አካውንት ሪፖርት ማድረግ ከፈለጉ፦
•ሪፖርት ማድረግ ወደፈለጉት አካውንት ይሂዱ፤
•ከዚያም በስተቀኝ ከላይ የሚታዩትን ሶስት ነጠብጣቦች (…) ይጫኑ፤
•ቀጥሎ “Report” የሚለውን ይጫኑ፤ ከዚያም መመሪያዎችን ይከተሉ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::