በሪቨርስ ኢሜጅ ሰርች የሞባይል መተግበርያዎች አማካኝነት ምስሎችን እንዴት መፈለግ ይቻላል?

በመጀመርያ እንደ “Search by Image” ያሉ የምስል ማሰሻ/መፈለግያ የሞባይል መተግበርያዎችን ስልክዎ ላይ ይጫኑ ወይም ድረ-ገፁን ይክፈቱ።  

1. መተግበርያውን በመክፈት ለማጣራት የሚፈልጉትን ምስል ያስገቡ። 

2. የሚያጣሩት ምስል የፎቶ ማስቀመጫ (gallery) ውስጥ ካለ Image Gallery የሚለውን ይምረጡ። 

3. ከዚያም ፎቶው ያለበትን የፋይል ማስቀመጫ (folder) ያስገቡ እና ምስሉን ይምረጡ።  

4. ከዛም የመፈልጊያ (🔎) ምልክቱን በመጫን ፍለጋውን ያስጀምሩ።  

5. በመጨረሻም የፍለጋውን ውጤት ያንብቡ፣ በዚህም ምስሉ መቼ እና በማን ከዚህ በፊት ቀርቦ እንደነበር ይረዳሉ። 

ቢያንስ እንዲህ ያሉ ቀላል የምስል ማሰሻዎችን ሳይጠቀሙ እና ሳያጣሩ አጠራጣሪ ምስሎችን ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቆጣጠር የድርሻዎን ይወጡ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::