የሞባይል ስልክ ቁጥርዎ ሰሞኑን ሾልኮ ከወጣው የፌስቡክ ዝርዝር ውስጥ ካለ እንዴት ማረጋገጥ ይችላሉ?

ሰሞኑን ከ530 ሚልዮን በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ዳታ (ስልክ፣ ኢሜይል ወዘተ) በጠላፊዎች ሾልኮ እንደወጣ ተሰምቷል፣ ከዚህ ውስጥ 12,000 ኢትዮጵያውያን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እንደሚገኙበትም ታውቋል።

ታድያ የእርስዎ ስልክ ወይም ኢሜይል እዚህ ዝርዝር ውስጥ ከተገኘ ማረጋገጫ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ጠይቀው ሊሆን ይችላል። Have I Been Pwned (https://haveibeenpwned.com/) የተባለ ድረ-ገፅ ይህን ማረጋገጥ ይችላል።

አጠቃቀሙ እንዲህ ነው: https://haveibeenpwned.com/ ድረ-ገፅን ሲከፍቱ የመፃፍያ/መፈለግያ ቦታ ያገኛሉ። ባዶ ቦታው ላይ ስልክዎን ወይም ኢሜይልዎን ያስገቡ። ከዛም “pwned?” የሚለውን ይጫኑ።

“Oh no- pwned” የሚል መልስ ካገኙ ስልክዎ ወይም ኢሜይልዎ ለጠላፊዎች ተጋልጦ ነበር ማለት ነው። “Good news- no pwnage found!” የሚል ምላሽ ካገኙ ለጠላፊዎች አልተጋለጡም ማለት ነው።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::