የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

በጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ላይ ጠንካራ ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስታወቀ።

የዴሞክራሲን ስርዓትን በሕግ ስርዓት ውስጥ ለመገንባት በጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ላይ ጠንካራ ቁጥጥር እንደሚደረግ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል። 

ምክር ቤቱ ያዘጋጀው የዴሞክራሲ ተቋማት በሆኑት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተርና የመገናኛ ብዙኃን የማሻሻያ የለውጥ ስራዎችን የተመለከተ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው። 

መገናኛ ብዙሃን ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጃ ለህብረተሰቡ እንዲደርስ በትጋት መስራት እንዳለባቸው ገልጸው፤ ምክር ቤቱም ክትትሉን ያጠናክራል ነው ያሉት። በተጀመረው የ2015 በጀት ዓመት በጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ላይ ጠንካራ ቁጥጥር እንደሚደረግ ያመለከቱት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ፤ ይህም የዴሞክራሲ ስርዓትን በሕግ ስርዓት ውስጥ ለመገንባት ያስችላል ብለዋል። 

Via FBC

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::