የበላይነህ ክንዴ ግሩፕን የንግድ ምልክትና ስያሜ በመጠቀም የተከፈተ የቴሌግራም ቻናል! 

የበላይነህ ክንዴ ግሩፕን የንግድ ምልክትና ስያሜ በመጠቀም በቅርቡ የተከፈተ የቴሌግራም ቻናል መኖሩን ተመልክተናል። ይህ “BelayNeh Kindie | በላይነህ ክንዴ ግሩፕ” የሚል ስያሜ ያለው የቴሌግራም ቻናል በአሁን ሰዐት 840 ተከታዮች ያሉት ሲሆን የስራ እድልንና በሚሊዮኖች የሚያስገኙ ሽልማቶችን ማዘጋጀቱን የሚገልጹ መልዕክቶችን ሲያጋራ አስተውለናል። 

ኢትዮጵያ ቼክ የዚህን የቴሌግራም ቻናል ትክክለኛነት በተመለከተ በላይነህ ክንዴ ግሩፕን ያነጋገረ ሲሆን የድርጅቱ የኮሚኬሽን ክፍል ቻናሉ የነሱ አለመሆኑን አሳውቀውናል። በተጨማሪም በላይነህ ክንዴ ግሩፕ ምንም አይነት የቴሌግራም ቻናል እንደሌለው ገልጿል። 

ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ ገጾችን እና አካውንቶችን ባለመከተል ከሀሰተኛና ከተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት እራሳችንን እንጠብቅ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::