በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች አውቶብስ ላይ አደጋ መድረሱንና የሰው ህይወት ማለፉን የሚገልፅ የሃሰት መረጃ እየተሰራጨ ነበር

“ማምሻውን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የድርጅታችን አውቶብስ ላይ አደጋ መድረሱንና የሰው ህይወት ማለፉን የሚገልፅ የሃሰት መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል”— አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት

ድርጅቱ እንዳለው “መረጃው ከእውነት የራቀ እና ከሁለት አመታት በፊት የተፈጠረውን አደጋ ዛሬ የተፈጠረ በማስመሰል የሃሰት እና የሽብር መረጃ ለማህበረሰቡ የማዛመት ስራ እየተሰራ መሆኑን ማህበረሰቡ እንዲያውቅ እንዲሁም ሃገራችን የገጠማትን ፈተና የተዛባ መረጃ በመንዛት ግጭቱን ለማባባስና የሃሰት ወሬዎችን በማናፈስ ሁከት ለመፍጠር የሚጥሩ በርካታ ግለሰቦችም ሆነ ሚዲያዎች ስላሉ ሁሉም ሰው ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማጋራትም ሆነ በመረጃዎቹ ከመረበሽ መቆጠብ እንዳለበት እና አላስፈላጊ ሽብር ለመፍጠር የሃሰት መረጃ የምታሰራጩ ሚዲያዎችም ሆነ ግለሰቦች ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ለማሳሰብ እንወዳለን” ብሏል።።

Via አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ኮሚኒኬሽን ቢሮ

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::