ፌስቡክ፣ ሜሴንጀር፣ ዋትስአፕ እና ኢንስታግራም በአለም ዙርያ መስራት አቁመዋል!

ችግሩ ምን እንደሆነ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን በርካታ አለም አቀፍ ሚድያዎች ጉዳዩን እየዘገቡት ይገኛል።

Update:

“ችግሩ የተከሰተው ስህተት በነበረበት የጥገና ለውጥ ምክንያት ነው”— ፌስቡክ

ለስድስት ሰአታት ገደማ ተቋርጦ የነበረው የፌስቡክ፣ ሜሴንጀር፣ ዋትስአፕ እና ኢንስታግራም አገልግሎት ዳግም ስራ ጀምሯል። በፌስቡክ ስር የሚተዳደሩት እነዚህ መተግበርያዎች በመቋረጣቸው ምክንያት በአለም ዙርያ 10.6 ሚልዮን ሪፖርቶች መደረጋቸውን Downdetector አሳውቋል።

በትልልቅ ድርጅቶች ደረጃ በዚህ መጠን መቋረጥ ያልተለመደ ቢሆንም በ2019 ፌስቡክ እና በስሩ ያሉ ሌሎች መተግበርያዎች ከ14 ሰአታት በላይ ተቋርጠው ነበር። የአሁኑ መቋረጥ ፌስቡክ ላይ በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ጉዳት እንዳደረሰ ተጠቁሟል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::