በኢትዮጵያ የፌስቡክ፣ ፌስቡክ ሜሴንጀር፣ ቴሌግራም እና ዋትስአፕ አገልግሎቶች ተቋርጠዋል! 

በኢትዮጵያ የፌስቡክ እና ፌስቡክ ሚሴንጀር እንዲሁም ቴሌግራምና ዋትስአፕ የተወሰኑ አገልግሎቶች መቋረጣቸውን ተመልክተናል። 

ኔትብሎክስ የተሰኝዉ አለም አቀፉ የኢንተርኔት ክትትል ተቋምም ይህን በመረጃ አስደግፎ አውጥቷል። አገልግሎቶቹ ዛሬ ከሰአት ጀምሮ እንደተቋረጡም ተቋሙ በድረ-ገጹ አስነብቧል። 

የአገልግሎቶቹ መቋረጥ ምክንያትም “የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተሰርቆ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተለቋል” የሚሉ መረጃዎች መዘዋወር ከጀመሩ በኋላ እንደሆነም ተገልጿል። 

ይሁንና የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ከሰአት በሰጡት መግለጫ የፈተናው ሂደት በሰላማዊ መንገድ መከናወኑን ገልጸው “ምንም ዓይነት ፈተና፣ በማንም፣ በምንም፣ በየትም ቦታ አልተሰረቀም” ብለዋል። ነገር ግን ፈተናውን ፎቶ በማንሳት የመኮረጅ ሙከራ ያደረጉ አራት ተማሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉንም ተናግረዋል። 

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ከኢመደኤ እና ኢትዮ ቴሌኮም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሙከራ ቢያደርግም እስካሁን አልተሳካም። አሁንም ሙከራ እያረግን ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ስናገኝ ይዘን እንቀርባለን።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::