የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ሶሻል ሚድያ ላይ ሲዘዋወር በነበረ ምስል ዙርያ ያወጣው ማብራርያ! 

ከትናንትና ምሽት ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ያመሩ በነበሩ የቀይ መስቀል ማህበር ተሽከርካሪዎች ላይ በአፋር ክልል በተደረገ ፍተሻ በርከት ያለ ጥሬ ገንዘብ ስለመያዙ የሚገልጹ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ተሰራጭተዋል። 

ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሚከተለውን አጭር ማብራሪያ ሰጥቷል። 

“በምስሉ ላይ የሚታየው ገንዘብ ህገወጥ እንደሆነ የሚገልጽ መልዕክት በማህበርዊ ሚዲያዎች እየተዘዋወረ መሆኑን ተገንዝበናል። ነገር ግን ምስሉ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አምስት ተሽከርካሪዎችን ባካተተው ኮንቮይ ከሁለት ሳምንት በፊት በአፋር ክልል በነበረው ፍተሻ ወቅት የተነሳ ሲሆን በምስሉ ላይ የሚታዩት ቁሳቁሶች በሙሉ፣ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታና የህክምና ቁሶችንም ያካትታል፣ የሚመለከታቸው የፌድራልና የክልል መንግስት አካላት በቅድሚያ እንዲያውቋቸው ተደርገውና ፈቃድ ተገኝቶባቸው የተጓጓዙ ናቸው። ቁሳቁሶቹና ገንዘቡ ድርጅታችን፣ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች እንደሚያደርገው ሁሉ፣ ለሚሰጠው የሰብዐዊ አገልግሎት ተግባር የሚውል ነው። ሁሉም ቁሳቁሶች መቀሌ የሚገኘው ቢሯችን ደርሰዋል። ድርጅታችን ጥሬ ገንዘብ ያጓጓዘው የባንክ አገልግሎት ባለመኖሩ ነው”

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::