ፓሪስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሱዳን ፖስት የተባለ ሚዲያ ያወጣው ዜና አሳሳች መሆኑን በማህበራዊ ሚዲያ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል!

በፈረንሳይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማክሰኞ፣ የካቲት 1 2014 ከፈረንሳይ የሴኔት አባላት ጋር መገናኘቱን ገልጾ ባወጣው ፅሁፍ መንግስት ለሰላም መስፈን ያለውን ቁርጠኝነት “የብሄራዊ የውይይት ኮሚሽን በማቋቋም እና ከፍተኛ የፖለቲካ ሰዎችን ከእስር እንዲፈቱ በማድረግ እየሠራ ነው” ይላል።

በሌላ በኩል ሱዳን ፖስት በዜናው “ኢትዮጵያ ተጨማሪ ታዋቂ የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ልትፈታ ነው ” ይላል።

ኤምባሲው ትናንት ባወጣው መግለጫ ሱዳን ፖስት ይህንን ዜና አሳሳች በሆነ መልኩ ዘግቦታል በማለት “ወደፊት ስለሚደረግ [ከእስር] መፍታት በዚህ ስብሰባ ላይ አልተነሳም” ብሏል።

ኢትዮጵያ ቼክም እንደተመለከተው የኤምባሲው ፅሁፍ ለትርጉም ክፍት ቢሆንም “ኢትዮጵያ ተጨማሪ ታዋቂ የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ልትፈታ ነው” ተብሎ እንደ ቀጥተኛ ትርጉም በሱዳን ፖስት የቀረበው ዜና አሳሳች መሆኑን ተመልክቷል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::