የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፌስቡክ ገጹ ዛሬ ለተወሰነ ጊዜ ከቁጥጥሩ ውጭ ወጥቶ እንደነበር እንደነበር አስታወቀ!

የፌስቡክ ገጹ ከቁጥጥሩ ውጭ ወጥቶ በነበረበት ሰዐትም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ የተላለፈ ነው የተባለ ሀሠተኛ መልዕክት ተለጥፎ እንደነበር አየር መንገዱ አስታወቋል።

አየር መንገዱ ጨምሮ እንደገለጸው ዋና ስራ አስፈጻሚው በኢትዮጵያ አየር መንገድ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይሁን በሌላ መንገድ ያስተላለፉት ምንም አይነት መልዕክት አልነበረም። ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ በነበረው የፌስቡክ ገጽም ተለጥፎ የነበረው መልዕክት የዋና ስራ አስፈጻሚውንም ሆነ አየር መንገዱን እንደማይወክል አስታውቋል።

ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ የነበረውን የፌስቡክ ገጽ በአሁኑ ሰዐት በአየር መንገዱ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ተገልጿል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::