ውድ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮች፣ 

በቅርብ ሳምንታት ፊያስ ስለተባለ እንቅስቃሴ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ቋንቋዎች መረጃዎችን አድርሰናችሁ ነበር። በነዚህ መረጃዎች ላይ እንቅስቃሴው እውቅና እንደሌለው፣ መንግስት ክትትል እያረገ እንደነበርና ጥንቃቄ እንዳይለያችሁ አሳስበን ነበር። 

እንደዛም ሆኖ በርካታ ግለሰቦች እንቅስቃሴው ላይ ተሳታፊ ሆነው ነበር፣ አሁን እንዳረጋገጥነው ደግሞ ስራውን ሲመሩ የነበሩ ግለሰቦች ደብዛቸውን አጥፍተዋል፣ በርካቶችም ገንዘባቸውን አጥተዋል። 

እውቅና የሌላቸው ድርጅቶችን፣ ምርት እና አገልግሎት የሌላቸው ተቋማትን እና ምንም ስራ ሳይሰራ ገንዘብ ታገኛላችሁ የሚሉ እንቅስቃሴዎችን በጥርጣሬ እንድትመለከቱ በድጋሜ መልእክታችንን እናስተላልፋለን። 

https://t.me/ethiopiacheck/1196 

https://t.me/ethiopiacheck/1288 

https://t.me/ethiopiacheck/1292

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::