ፌስቡክ ራሱን “የኦሮሞ ነፃነት ጦር” የሚለውን፣ በኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ “ኦነግ ሸኔ” በመባል ከሚጠራው ድርጅት ጋር ትስስር ያላቸውን ግለሰቦች ስምና ቃላት በፕላትፎርሙ መፈልጊያ (Search) ላይ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማስጠንቀቂያ የታከለበት እቀባ መጣሉን ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል።

ፌስቡክ ከወራት በፊት “አደገኛ ናቸው” ያላቸውን ግለሰቦችና ቡድኖች (Dangerous Individuals and Organizations) ፕላትፎርሙን እንዳይጠቀሙ የሚያበረታታ ፖሊሲ ማውጣቱ የሚታወስ ሲሆን ከኢትዮጵያ ይህ ድርጅት እና “አባ ቶርቤ” በመባል የሚታወቁ ቡድኖች ላይ ይህ ፖሊስ ተፈጻሚ እንደሚሆን አስታውቆ ነበር።

ፌስቡክ “አደገኛ ግለሰቦችና ቡድኖች” ያላቸውን አካላት በተመለተ ባወጣው ፖሊሲ “መንግስታዊ ያልሆኑ ነውጠኛ ቡድኖች” (Violent Non-State Actors) መሪዎች፣ ታዋቂ አባላት እንዲሁም ተወካዮችን አካውንቶችና ገጾች የማገድ እርምጃ እንደሚተገብር አብራርቶ ነበር። በተጨማሪም የድርጅቶቹን እንቅስቃሴ የሚያበረታቱ ይዘቶችን እንደማያስተናግድ ገልጾ ነበር።

ይህንን ተከትሎም ፌስቡክ የድርጅቶችንና መሪዎች ስምና እንዲሁም ተያያዥ ቃላቶችን በፕላትፎርሙ የመፈለጊያ አገልግሎት ላይ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማስጠንቀቂያ የታከለበት እቀባ መጣሉን ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል። የፕላትፎርሙ ተጠቃሚዎች ከላይ የተጠቀሱ ስሞችንና ቃላትን በፕላትፎርሙ መፈለጊያ አስገብተው ለማሰስ ከፈለጉ ከፖሊሲው ጋር የሚጣረስ መሆኑን የሚገልፅ ማስጠንቀቂያ እንደሚሰጥ ማየት ይቻላል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::