የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የፌስቡክ ገጽ ተጠልፏል!

ከ130 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የኢንስቲትዩቱ የፌስቡክ ገጽ መጠለፉን ኢንስቲትዩቱ ዛሬ ከሰዕት ለሚዲያ አካላት በላከዉ መግለጫ አስታዉቋል።

ተቋሙ “EPHI Ethiopia ስለተጠለፈ እስከሚስተካከል ድረስ በዚህ ገፅ የሚወጡ መረጃዎች ከኢንስቲትዩቱ ዕውቅና ውጭ መሆናቸውን እናስታውቃለን” ብሏል።

በዛሬዉ እለት የተለያዩ ቪድዮዎች የኢንስቲትዩቱ የፌስቡክ ገጽ ላይ ሲለጠፉ መቆየታቸዉን ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፌስቡክ ገጽ በተለይ የኮቪድ-19 ወረርሺኝን ተከትሎ ስለ በሽታዉ ወቅታዊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ሲያደርስ መቆየቱ ይታወቃል።

በሌላ በኩል ከሰሞኑ የተለያዩ ተቋማት ላይ የሚደርሱ መሰል ጥቃቶች እየተበራከቱ በመሆናቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን ደህንነት በሚገባ መጠበቅ ትኩረት ሊሰጠዉ የሚገባ ጉዳይ ነዉ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::