የአዲስ አበባ ከተማ የሕንጻዎችን ቀለም በተመለከተ በከተማ አስተዳደሩ ዛሬ የወጡ እርስ በርስ የሚጣረሱ መረጃዎች! 

ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ህንፃዎች ግራጫ ቀለም ሊቀቡ እንደሆነ በሪፖርተር ጋዜጣ መረጃ ወጥቶ ነበር፣ ይህ መረጃም ማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት የተሰራጨ ሲሆን የብዙዎች መነጋገርያም ሆኖ ሰንብቷል። 

ይሁንና ዛሬ ጠዋት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ መረጃው “ሀሰት” ነው ብለው ተናግረው ነበር። ኃላፊው “በቅርቡ በጉዳዩ ላይ ከባለሀብቶች ጋር ውይይት ተደርጎ ነበቶር፣ ይህን መነሻ አድርገው አንዳንድ ግለሰቦች ለግራጫ ቀለም የመሰላ ቸውን ትርጓሜ ሲሰጡ ተመልክተናል፣ ጉዳዩ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እንደሚዘዋወረው ተግባር ላይ የዋለ ሳይሆን ገና ለምክክር የቀረበ ነው” ብለው ከአራት ሰአት በፊት ተናግረው ነበር። 

ይሁንና ከደቂቃዎች በፊት የከተማ አስተዳደሩ ለከተማዋ የሚስማሙ 13 ዓይነት ቀለማት መለየታቸውን ገልጿል። “በዚህ መሰረት በሌሎች ሀገራት እንደሚደረገው ለከተማዋ በመለያነት ከተመረጡ ቀለማት መካከል የሕንጻ ባለንብረቶች የሚመርጡትን ወስደው የመጠቀም መብት ያላቸው ሲሆን ይህ አሠራር በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ ክፍለ ከተሞች ተጀምሮ ወደ ትግበራ ተገብቷል” በማለት የተመረጡትን ቀለሞች አስቀምጧል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::