ህገወጥ የገንዘብ መላኪያ ድረ -ገፆች መከፈት ጀምረዋልና ይጠንቀቁ!

(ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘ መረጃ)

የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራችን በመካሄድ ላይ ባለው ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የምትልኩትን ገንዘብ ህጋዊ ለማረግና የተበታተነ የገንዘብ አላላክን በአንድ ቋት ለመድረግ እንዲቻል https://eyezonethiopia.com/ አማካኝነት በማሰባሰብ ላይ እንደሆነና እያደረጋችሁት ያለው ድጋፍም በግልፅ የሚታይና ለተጎጂ የህብረተሰብ ክፍል እንደሚደርስ ይታወቃል።

ሆኖም አንዳንድ አጭበርባሪዎች የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያዎችና ድረ-ገጾች የተሻለ የመዘርዘሪያ እና የመላኪያ ዋጋ እናቀርባለን በማለት መተግበሪያዎችን እየሰሩ ድረ-ገፅ ላይ እየለቀቁ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እያሳሰብን እንዲህ አይነቱ የማጭበርበር ስራ እናንተ የዳያስፖራ ወገኖቻችን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የምታደርጉትን ድጋፍ ለማስተጓጎልና ለሀገር የሚጠቅመውን የውጭ ምንዛሬም ወደራሳቸው ሀገር በማስቀረትና ህጋዊ ያልሆነ የገንዘብ ዝውውርን ሀገር ውስጥ በማስፋፋት ሀገርን የሚጎዳ እንቅስቃሴ ለማድረግ ላይ ጥረት እንደሚያደርጉ ተገንዝበናል።

እነዚህ አካላት በተለይ በቅርቡ ወደ ሀገራችሁ የምትመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ኢላማ አድርገው እየተንቀሳቀሱ ሲሆን ህጋዊ ያልሆኑ የገንዘብ አዘዋዋሪ ተቋማትን ባለመጠቀም ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን እንድትከላከሉ በዚህ አጋጣሚ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::