አርቲስት ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲ ጂ) የፌስቡክ ገጿ መጠለፉን አስታወቀች!

አርቲስቷ ከ219 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትና ቬሪፋይድ የሆነዉ የፌስቡክ ገጿ (https://www.facebook.com/Goahear) መጠለፉን በኢንስታግራም አካዉንቷ ባሰፈረችዉ ጽሁፍ አስታዉቃለች።

“የፌስቡክ ገጼ መጠለፉን ሳሳዉቃቹ እያዘንኩ ነዉ። ይህን ጉዳይ ለመፍታት እየሰራን እንገኛለን። ከተጠለፈዉ ፌስቡክ ገጼም ሆነ ትክክለኛ ካልሆኑ (unofficial) አካዉንቶች የሚተላለፉ መልዕክቶች የኔ አይደሉም” ብላለች።

የአርቲስቷ ፌስቡክ ገጽ ፕሮፋይል ምስል ከአስር ቀናት በፊት መቀየሩንና ከዛ ወዲህም የተለያዩ መልዕክቶች በገጹ ላይ መለጠፋቸዉን ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል።

የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን ደህንነት በሚገባ ለመጠበቅ ስለሚረዱን ዘዴዎችና መሰል መረጃዎችን ለማግኘት፦

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::