አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሰሞኑን የሚጠቀሙት አውሮፕላን ጉዳይ!

አንዳንድ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮች የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከሰሞኑ የሚጠቀሙበትን አውሮፕላንን በተመለከተ ጥያቄ አቅርበውልናል።

ከሰሞኑ እንደተመለከትነው አቶ ሽመልስ ወደ ጅግጅጋ፣ አሶሳ እና ጋምቤላ ሲጓዙ የ East African Aviation ንብረት የሆነ እና King Air 350 የተባለ አነስተኛ አውሮፕላን የተጠቀሙ ሲሆን ወደ ባህር ዳር ሲሄዱ ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራን ተጠቅመዋል።

East African Aviation የተመሰረተው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ39 አመታት በአብራሪነት ባገለገሉት ካፕቴን ሙላት ለምለም ሲሆን የቻርተር በረራዎች፣ የአየር አምቡላንስ አገልግሎት እንዲሁም የአብራሪነት ስልጠና አገልግሎት ይሰጣል።

ኢትዮጵያ ቼክ የመንግስት ሀላፊዎቹ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስር ከሚከናወኑ መደበኛ በረራዎች ይልቅ ብዙ ግዜ እጅግ ውድ እንደሆኑ የሚነገርላቸውን የቻርተር በረራዎች ለምን እንደተጠቀሙ ለማወቅ ያደረገው ጥረት ለግዜው አልተሳካም።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::