ፌስቡክ የግሩፕ አስተናባሪዎችን (Group Admins) የሚያግዝ ‘አድሚን አሲስት’ (Admin Assist) የተባለ አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች ማሻሻያዎችን ማድረጉን ገልጿል!

ይፋ የተደረጉት አገልግሎቶችና ማሻሻያዎች የግሩፕ አስተናባሪዎች የሚቆጣጠሯቸውን ግሩፖች ከሀሠተኛ መረጃ የጸዱ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀና ጤናማ እንዲሆኑ የሚያደርጉትን ጥረት ያግዛል ተብሏል።

‘አድሚን አሲስት’ ይከውናቸዋል ከተባሉ ተግባራት መካከል ሀሠተኛ መሆናቸው በሶስተኛ ወገን መረጃ አጣሪዎች (third party fact-checkers) የተጋለጡ መልዕክቶች በግሩፖች እንዳይጋሩ ማድረግ ይገኝበታል። ይህም በግሩፖች የሚታየውን የሀሠተኛ መረጃ ስርጭ ይቀንሳል ብሎ እንደሚያምን ፌስቡክ አስታውቋል።

እንዲሁም ማሻሻያ ከተደረገባቸው መካከል ‘ሚዩት’ (mute) የተሰኘው አገልግሎት የሚገኝበት ሲሆን አሁን ወደ ‘እገዳ’ (suspend) ከፍ እንዲል ተደረጓል። ይህም የግሩፕ አስተናባሪዎች የግሩፑ አባል የሆኑ አካውንቶችን በጊዜዊነት የማገድ ስልጣን ይሰጣቸዋል። እገዳ የተጣለበት የግሩፑ አባልም መልዕክት የማጋራት፣ ግብረመልስና ምላሽ የመስጠት፣ በግሩፕ ውይይቶች የመሳተፍና ሌሎችን መብቶች የሚያጣ ይሆናል።

በተጨማሪም አዲሶቹ አገልግሎቶች ወደ ግሩፕ የሚቀላቀሉ የፌስቡክ አካውንቶችን እንዲሁም የሚጋሩ ይዘቶች የሚያጠሉ (filter) ሲሆን ይህም የግሩፕ አስተናባሪዎችን ስራ በእጅጉ እንደሚያቀል ተገልጿል። (ለምሳሌ አዲስ የተከፈቱ አካውንቶች ግሩፑን ይቀላቀሉ ወይም ማስፈንጠሪያ የተያያዘባቸው መልዕክቶች በግሩፑ ይጋሩ የሚለውን የግሩፑን መስፈርቶች ተከትለው ያጠላሉ)።

የግሩፕ አስተናባሪዎች የነዚህ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ለመሆን የግሩፓቸውን ሴቲንግ ማዘመን (update ማረግ) ይጠበቅባቸዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::