የአርብ የሚድያ ዳሰሳ

ሐምሌ 15/2014

1. ከቀናት በኋላ በኬኒያ የሚደረገው ምርጫ ከጥላቻ መልዕክቶች፣ ከሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች የነጻ ለማድረግበቂ ዝግጅት ማድረጉን ሜታ በሳምንቱ አጋማሽ አስታውቋል። ለዚህም እንዲረዳው በኬኒያ የኦፕሽን ማዕከልማቋቋሙን፣ በሰው ሀይልና በቴክኖሎጅ እራሱን ማጠናከሩን፣ ከመርጃ አጣሪ ተቋማት ጋር ቅንጅት መፍጠሩንእንዲሁም የሚዲያ አጠቃቀም ንቃት (media litracy) ላይ ከሚሰሩ ተቋማት ጋር በትብብር መስራት መጀመሩንአብራርቷል። በቅድመ ምርጫው እስከ ሚያዚያ ወር መጨረሻ በነበሩ ስድስት ወራት ከፖሊሲዎቹ  ጋር ተቃርነዋልያላቸውን 79 ሺህ ይዘቶችን ማስወገዱን እንዲሁም ከግልጽነት ፖሊሲዎቹ (transparency policy) ጋርተጣርሰዋል ያላቸው 36 ሺህ የፖለቲካ ማስታወቂያዎች ላይ በሩን መዝጋቱን ገልጿል።

2. ሜታ፣ ትዊተር፣ ጎግል፣ ቲክቶክና ሌሎች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በኢንዶኔዥያ ለመንቀሳቀስ የሚያስችላቸውንምዝገባ መከወናቸውን ብሉምበርግ አስነብቧል። ኩባንያዎቹ ለመመዝገብ የተገደዱት የኢንዶኔዥያየኮሚኒኬሽንና ኢንፎርማቲክስ ሚንስቴር እሰከ ረቡዕ (ሐምሌ 13/2014 .) ተመዝግበው ፍቃድ ካላወጡበሀገሪቱ እንዳይሰሩ የዕገዳ እርምጃ እንደሚወስድ ካስጠነቀቀ በኃላ ነበር። ምዝገባውን ተከትሎ ኩባንያዎቹየኢንዶኔዥያን ህግ ተከትለው እንዲሰሩ የሚገደዱ ሲሆን በዚህ ከሀገሪቱ ህግ ጋር የሚጣረሱ ይዘቶችን በአራትሰዐታት ውስጥ ማንሳት ይጠበቅባቸዋል።

3. የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እስከ አምስት የሚደርሱ ፕሮፋይሎችን መክፈት የሚችሉበትን አሰራር ወደ ስራለማስገባት የሙከራ ትግበራ መጀመሩን የማህበራዊ መገናኛ ዘዴው ቃል አቀባይ ሊዮናርድ ላም አስታውቀዋል።በአዲሱ አሰራር የፌስቡክ ተጠቃሚዎች አዲስ አካውንት መክፈት ሳይጠበቅባቸው ተጨማሪ አራት ፕሮፋይሎችእንዲኖራቸው ያስችላል ተብሏል። በዚህም ተጠቃሚዎቹ አንዱን ፕሮፋይል ከወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ አንዱንፕሮፋይል ከስራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም በቀሪዎቹ ፕሮፋይሎች ከሌሎች ጋር ለመወዳጀትና መስተጋብርለመፍጠር ያስችላቸዋል። ተጨማሪዎቹ ፕሮፋይሎች ከዋናው አካውንት ጋር የሚቆራኙ ሲሆኑ ተጠቃሚዎቹየተለያዩ ስሞችንና የፕሮፋይ ምስሎችን መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል። ይህ አሰራር በፌስቡክ የሚደረጉመስተጋብሮችን የበለጠ እንደሚያነቃቃ ቃል አቀባዩ ተስፋቸውን ገልጸዋል።

4. አለም አቀፉ የጽንፈኛ ርዕዮተዓለሞች ተከላካይ ማዕከል (Global Center for Combating Extremist Ideology) ከቴሌግራም ጋር በመቀናጀት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 1.2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ጽንፈኛ ይዘቶችንናወደ ይዘቶቹ የሚያመሩ ማስፈንጠሪያዎች እንዲወገዱ ማድረጉን አስታውቋል። ማዕከሉና ቴሌግራም በይዘቶቹናበማስፈንጠሪያዎች ላይ እርምጃ የወሰዱት ከሰኔ ወር የመጀምሪያ ሳምንት እስከ ሀምሌ ወር ሁለተኛ ሳምንትመጀምሪያ ባሉት ጊዚያት መሆኑ ተጠቅሷል። ሁለቱ ተቋማት በትብብር ለመስራት የተስማሙት ባለፈው የካቲትወር ነበር።

5. በመጨረሻም፣ ሰኞ እለት በሞስኮ የሚገኝ አንድ ፍርድ ቤት ጎግል 370 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ለሩሲያመንግስት እንዲከፍል ብያኔ መስጠቱን ሮይተርስ ዘግቧል። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው የሀገሪቱየኮሚኒኬሽን ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤት በዩትዩብ አንጻር ክስ ከመሰረተ በኋላ ነበር። የኮሚኒኬሽን ተቆጣጣሪመስሪያ ቤቱ በጎግል ስር የሚተዳደረው ዩትዩብ ከሩሲያ ህግ የሚጣረሱ ይዘቶችን አላነሳም የሚል ክስ ነበርየመሰረተው። ጎግል ብይኑን በተመለከት እስካሁን ምላሽ አለመስጠቱ የተገለጸ ሲሆን ቅጣቱ በሩሲያ ገቢያከሚያገኘው ገቢ ቀላል የማይባለውን እንደሚያሳጣው ተዘግቧል። ጎግል በተመሳሳይ ክስ በታህሳስ ወር 100 ሚሊዮን ዶላር የተቀጣ ሲሆን በግንቦት ወር ለመስራት መቸገሩን በመግለጽ በሩሲያ የሚገኘውን ቢሮውንእንደሚዘጋ አስታውቆም ነበር።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::